Mission and Vision
የፖሊስ ኮሚሽን ራዕይ
የህብረተሰቡ ተሳትፎ በክልሉ ዘላቂ ሰላም ሰፍኖ ዜጎች ሰበአዊ መብታቸውና ነፃነታቸው ተከብሮላቸው ከግጭትና ከወንጀል ከአደጋ ስጋቶች
ነፃ ሆነው ፈጣንና ጥራት ያለው የፍትህ አገልግሎት ከጥሩ መስተንግዶ ጋር እያገኙ ኑሮአቸውን በሰላም ሲኖሩ ማየት
ተልዕኮ
ህብረተሰቡን በማደራጀትና በወንጀል መከላከል ተግባር ላይ በማሳተፍ የፖሊሱን የማስፈፀም አቅም በማጎልበትና በዘመናዊ
ቴክኖሎጅ በመታገዝ ወንጀልን ፣አደጋን፣ ህገ ወጥ እንቅስቃሴንም ሆነ ግጭቶችን ከነ መንሴኤው መከላከል
ሀገሪቱንና የክልሉን ህገ--መንግስት በመጣስ ስርአቱን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ማኛውም የተደራጅ ፀረ ሰላም ፀረ ዲሞክራሳዊና ፀረ ልማት
እንዲሁም ሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን በመከላከል ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ፡፡
ወንጀልን ሲካላከሉ ሆነ ምርመራ ሲጣራ ህግን ስርአትና ደንብን ሲያስከብርና ሰባአዊ መብቶችንና ነፃነቶችን አክብሮ ማስከበር፡፡
የፖሊስ ሙያ አገልግሎት በጥራትና በቅልጥፍና ከጥሩ መስተንግዶ ጋር ለህብረተሰቡ መስጠት
እሴት
-
ከተግባራት ሁሉ የወንጀል መከላከል ስራ ቅድሚያ መስጠት
-
የሀገሪቱንና የክልሉን ህገ--መንግስት ማክበረና ህገ--መንግስታዊ ስርአቱን መጠበቅ
-
ከአድሎና ከወገንተኝነት በመራቅ ለሁሉም ፍትሃዊ ፈጥንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት
-
ለህዝብ አቤቱታና ቅሬታ ፈጣን ምላሽ መስጠት ህዝቡን ማዳመጥ ማክበርና አብሮ በመስራትና የእለት ተግባር አካል ማድረግ
-
ወንጀልን በመጥላት የእድገት ፀር ሙስና ብልሹ ምግባሮችን ማስወገድ
-
ለአካባቢያዊ ችግር አከባባዊ መፍትሄ ማፍለቅ
-
በህግ በላይነት ማመን
-
አሳታፊነት ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን መቀበል
-
ቅንነት በከፍተኛ ደረጃ ማረጋገጥ መልካም ስነ-- ምግባር መከተል
-
ለሰዎች ህይወት ጥበቃ ከፍተኛ ዋጋ መስጠት በሰባአዊነት ማመን
-
ፍትሃዊነት፣ ታማኝነት ፣ትሁትነት ፣ሚስጥር ጠባቂነት
-
ለሁሉም የስራ እንቅስቃሴዎች የሙያ ቁርጠኝነት ማስፈን
-
በቡድን አሰራር ማመን
-
በእቅድ መመራት
-
ለውጥ መቀበልና መስጠት